Till Tema modersmål

Tema modersmål - amhariska

amhariska

የስዌን ቆርኪ

Skriv ut

የስዌን ቆርኪ

Swen_korki_1ብርቅየው የሰዌን ቆርኪ በኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙት ሰባት ጡት አጥቢ እንሰሳት አንዱ ነው። ቆርኪ ከትከሻው ከፍ ብሎ ከቂጡ ዝቅ ያለ ሲሆን ከአፉም ሾጣጣ ነው። የሰዌን ቆርኪ ከሌሎቹ አገሮች ቆርኪዎች የሚለየው በቀለሙ ነው። ቀለሙም ቸኮሌታማ ሲሆን ከበስተኋላው ነፃ ያለ ነው። ይህ እንሰሳ በአማካኝ የወንዱ ክብደት 150 እስከ 180 ኪሎ ግራም ይደርሳል። ሴቷ ቆርኪ ከወንዱ በመጠን ታንሳለች።

 ሰንቀሌ ፓርክ ውስጥ የሰዌን ቆርኪ ብዛት ከ700 እስከ 800 ይገመታል። የሰዌን ቆርኪ አደረጃጀታቸው በቡድን ሲሆን ቡድን የሚሰሩትም ሴቶች ለብቻ፣ ወንዶች ለብቻ እንዲሁም ወንድ በተናጠል።

የሰዌን ቆርኪዎች የሚመገቡት እስቪስተን የሚባል የሳር ዝርያ ነው።

ሰንቀሌ ፓርክ የተቋቋመውም ብርቅየውን የሰሜን ቆርኪን ከእልቂት ለመታደግ ነው።