Till Tema modersmål

Tema modersmål - amhariska

amhariska

ባህልና ቅርሳቅርሶች

አፈወርቅ ተክሌ

Skriv ut

ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

Afewerk_Tekle

እጅግ የተከበሩት የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ባደረባቸው ህመም ምክንያት አረፉ። በህይወት ዘመናቸው በሰሯቸው ስራዎች በርከት ያሉ ሽልማቶችን በአለም አቀፍ ደረጃ የተሸለሙ ሲሆን በአለማችን የህይወት ታሪካቸው ከየአገራቸው ሰንደቅ አላማ ጋር ወደ ጨረቃ በመወሰድ ከተቀበረላቸው የአለማችን ሁለት መቶ እውቅ መሪዎች እና ሊቃውንቶች አንዱ ነበሩ።

አፈወርቅ ተክሌ 

Läs mer...
 

አዲስ አመት

Skriv ut

እንኳን ለዘመን መለወጫው በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
መጭው 2004 የደስታ፣የጤንነት፣ የሰላም እንዲሁም የብልጽግና እንዲሆን እንመኛለን።

New_year

 

የቡሔ በአል አከባበር

Skriv ut

ቡሔ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበር በዓል ነው።

Buhie2የቡሔ በአል አከባበር በኢትዮጵያ ውስጥ ባህላዊም ሐይማኖታዊም ነው። በባህላዊ ስሙ ቡሄ ሲባል በሐይማኖታዊ ደግሞ ደብረታቦር በመባል ይታወቃል።

እየሱስክርስቶስ ያቆብን፣ ጴጥሮስን እና ዮሐንስን በመያዝ ወደረጅሙ ታቦር ወደ ተባለው ተራራ ይወጣል። ከዚያም መለኮ ተበብርሐን ተገጸ በፊታቸውም የእየሱስክርስቶስ ፊት እንደ ብርሐን በራ ልብሱም እንደብርሐን ነጭ ሆነ እንዲሁም ኤሊያስ እና ሙሴ ከእሱ ጋር ሲነጋገሩ ታያቸው። ጴጥሮስም እንዲህ አለ ጌታ ሆይ ብትወድ ለኛ በዚህ መሆንህ መልካም ነው ሶስት ዳስ በዚህ እንሥራ አንዱን ላንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ አለው ይህን ሲናገር ደመና ጋረዳቸው በደመናው ውስጥም ድምጽ ተሰማ

Läs mer...
 

ባህላዊ ምግቦች

Skriv ut

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምግብ እንጀራና ወጥ ነው። ወጥ ከተለያዩ ቅመማ ቅመሞች ተቀምሞ የሚሰራ ሲሆን እንጀራ ደግሞ ጤፍ ከሚባል እህል የሚዘጋጅ ነው። ብዙ የወጥ አይነቶች አሉ ለምሳሌ: የሥጋ፣ የድንች፣ የምስር፣ የዶሮ፣ አልጫና ቀይ ወጥ፣ የጎመን ወዘተ።

እንጀራ ለገበታ ሲቀርብ በትሪ ሲሆን ብዙ ጊዜ ባህላዊ መጠጦች ጠጅና ጠላ አብረው ይቀርባሉ። የቤተሰብ አባላት በአንድ ላይ ተሰብስበው በትሪ ይመገባሉ ይህም እንደ አባቶቻችን አባባል የሚገልፀው ፍቅርና አንድነትን ነው።

Enjera_betri

ባህላዊ የእንጀራ አገጋገር ይህን ይመስላል።

Läs mer...
 

ቡና

Skriv ut
ቡና
ቡና መጀመርያ የታወቀው በኢትዮጵያ ሲሆን የእንግሊዝኛው ስሙ (coffee /ኮፊ/ ) የመጣው ከድሮው ከፋ መንግስት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ። በመጀመርያ ያገኘው ሰው ካልዲ የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ እረኛ ፍየሎቹ ፍሬውን በልተው ሲጨፍሩበት ነበረ ይባላል። ቡና ወደ የመን የገባው በአክሱም መንግሥት ዘመን በ 517 ዓ.ም. አካባቢ ነበር። ቡና ወደ አውሮፓ መጀመርያ በ16ኛ ክፍለ ዘመን ያስገቡት ነጋዴዎች ከቬኒዝ ጣልያ ነበሩ።  በ1592 ዓ.ም. የሮማ ፓፓ 8 ቄሌመንጦስ ስላጸደቁት በቶሎ ዘመናዊ መጠጥ ሆነ። የመጀመርያው ቡና ቤት በአውሮፓ በጣልያ በ1637 ዓ.ም. ተከፈተ። አረቦች ግን የቡና ተክል ከአረብ ዓለም እንዲወጣ ባይፈቅዱም፣ በ1600-1650 ዓ.ም. ገዳማ አንድ ሃጂ ከሕንድ ስሙም ባባ ቡዳን ከሞቃ የመን ወጥቶ በስውር የቡና ዘር ይዞ ወደ ሚሶር ሕንድ አገር ተመለሰና ተክሉን እዚያ አበቀለው።  በ1608 ዓ.ም. የሆላንድ ሰዎች ወደ አደን መጥተው ለምለም የቡና ዘር ይዘው ወደ አገራቸው ተመለሡ። በ1690ዎቹ በሆላንድ ቅኝ አገሮች በጃቫ (ዛሬ ኢንዶኔዥያ) እና በሱሪናም (ደቡብ አሜሪካ) ያስፋፉት ጀመር። (ውክፒድያ)
http://www.hoboes.com/Politics/Prohibition/Notes/Coffee/
1 Bunna 1