የአመቱ አገር አቀፍ የአማርኛ መምህራን ስብሰባ በማርዬሀምን(Mariehamn) በ2011/05/16 በጥሩ ሁኔታ ተከናውኗል።
በስብሰባው ላይ ወደ 14 የሚሆኑ መምህራኖች ከመላው የስዊድን ክፍል የተገኙ ሲሆን በተለያዩ ነጥቦችም ላይ ተወያይተዋል።
የመወያያ ነጥቦች የነበሩት፡
- የትምህርት መገልገያዎች የሚሻሻሉበትን መንገድ መፈለግ።
- የትምህርት እቅድን በአገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ እሚሆንበትን መንገድ መቀየስ
- መምህራኖች በጋራ የሚሰሩበትን አንድ መድረክን መፍጠር
- የበለጠ ወላጅን ያሳተፈ የጋራ ትብብርን መፍጠር
- ተጨማሪ መፅሐፍቶችን ማዘጋጀት
- የኢኮኖሚ እገዛ የሚገኝበትን መንገድ ማፈላለግ
- ስለ አዲሱ የትምህርት ደንብ በመወያየት እቅዱ ግቡን እንዲመታ መደረግ ስለሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች እና ተግባራዊነቱ ነበር።
ወዘተ











