Till Tema modersmål

Tema modersmål - amhariska

amhariska

የእውቀት መመዘኛ ለወላጅ ግንዛቤ

Skriv ut

 የእውቀት መመዘኛ ለወላጅ ግንዛቤ

Kunskapskrav för betyget E i slutet av årskurs 6

  • ተማሪው ለዕድሜ ደረጃው የሚመጥኑ ጽሁፎችን ማንበብ መቻሉ፤
  • የተለያዩ ያነባበብ ስሌቶችን በቀላሉ ተግባር ሊይ ማዋሉ፤
  • ቀላልና አግባባዊ የሆኑ ማጠቃለያዎችን መስጠት መቻሉ፤
  • በቀላል ቋንቋ ሀሳቡን በጽሁፍ መግለጽ መቻሉ፤
  • ዘወትራዊ የሆኑ/ሁለታዊ/ እና ለደረጃው የሚመጥኑ ቃላትን በትክክል መጻፍ መቻሉ፤
  • በአፍ መፍቻ ቋንቋውና በስዊድንኛ መካከል ቀላል የልዩነትና የአንድነት ንፅፅር ማድረግ መቻሉ፤
  • ሀሳቡን በቀላል መንገድ በቃል መግለጽ መቻሉ፤

 Kunskapskrav för betyget D i slutet av årskurs 6

  • ይህን ውጤት ለማግኘት የ E መስፈርቶችን ወደ C የሚያስተላልፉ የተወሰኑ ችሎታዎችን ማሟላት ይጠበቅበታል፤

 Kunskapskrav för betyget C i slutet av årskurs 6

  • ለዕድሜ ደረጃው የሚመጥኑ ጽሁፎችን ከመጀመሪያው ሻል ባለመንገድና የተወሰነ ዓላማን ከግብ ለማድረስ ማንበብ መቻሉ፤
  • የተለያዩ ጽሁፎችን ይዘት በዳበረ መንገድ ለማጠቃለል መቻሉ፤
  • የጽሁፎችን ይዘት አንብቦ መረዳት መቻሉ፤
  • ተማሪው ከአፍ መፍቻ ቋንቋው ባህርይ በመነሳት በተደጋጋሚ የሚጠቀምባቸውን ቃላት በትክክለ መጻፍ መቻሉ፤
  • በውይይት ጊዜ ጥያቄ መጠየቅና የራሱን አስተያየት ማንጸባረቅ መቻሉ፤
  • ዕለታዊ ሁኔታዎችን በግልጽ መተረክ መቻሉ፤

 

Kunskapskrav för betyget B i slutet av årskurs 6

በዚህ ደረጃ የ C መስፈርቶች መሟላት አለባቸው፤ ወደ A የሚወስዱ ከፊል መመዘኛዎችም መሟላት ይጠበቅባቸዋል።

Kunskapskrav för betyget A i slutet av årskurs 6

  • ተማሪው ከቀዳሚው ደረጃ በጣም ሻል ባለ መንገድ አንብቦ መረዳት መቻል ይጠበቅበታል።
  • የተለያዩ አላማዎችን ከግብ ለማድረስ በሚያስችል መልኩ የአንድን ጽሁፍ ይዘት መርምሮ መረዳት ይጠበቅበታል።
  • እጅግ የዳበረ የማጠቃለያ ሐሳብ የማቅረብ ችልታም ሊኖረው ይገባል።
  •  የአንብቦ መረዳት ችሎታው ከቀዳሚዎቹ ደረጃዎች በጣም የላቀ መሆን ይኖርበታል።
  • በደንብ የበለጸጉ ማጠቃለያዎችን ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  • ሐሳቡን በተገቢው መንገድ በጽሁፍ ማስተላለፍ መቻል አለበት።
  • በውይይት ጊዜ ተዛማጅ ስለሆኑ ሀሳቦች ምንነት በደንብ ማስረዳት ይጠበቅበታል።
  • ቀደም ያለ ልምዱን መሰረት በማድረግ ምክንያታዊ የሆነ ገለጻ ማቅረብ ይጠበቅበታል። በተለይም ሐገራዊ እና ቋንቋዊ ማለትም አማርኛዊ የሆኑ እሴቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምክንያታዊ የሆኑ ትንታኔዎችን መስጠትና በግልጽ ማስረዳት ይኖርበታል።

 Kunskapskrav för betyget E i slutet av årskurs 9

  • ተማሪው የተለያዩ ጽሁፎችን ያለችግር በሚገባ ማንበብ መቻል ይኖርበታል። የተለያዩ ያነባበብ ስልቶችንም እንደጽሁፎቹ አይነትና እንደተጻፉበት አላማ እየለያየ ተግባር ላይ ማዋል ይጠበቅበታል።
  • የተለያዩ ጽሁፎችን ይዘት ቀለል ባለ መሌኩ ማጠቃለልና ዋና ሀሳቦቻቸውን መተቸት መቻል ይጠበቅበታል።
  • ቀደም ያለ ልምዱን መሰረት በማድረግ ምክንያታዊ እና አሳማኝ አስተያየቶችን መሰንዘር ይኖርበታል።
  • ሌላው አንባቢ ሊረዳ በሚችል መልኩ ያጻጻፍ ስልቶችን እየቀያየረ የተለያዩ ጽሁፎችን ማቀናበር ይኖርበታል። ጽሁፎቹም ቀለል ያለ የገላጭና የተራኪ ባህርይ የሚታይባቸው ሊሆኑ ይገባል።
  • ተማሪው ሀሳቡን በተገቢው መንገድ በቃል ማስተላለፍ ይጠበቅበታል።
  • ጥያቄ የመጠየቅና ሀሳብ የመሰንዘር ችሎታ ሊኖረው ይገባል።
  • ቀለል ባለ መንገድ ቃላዊ ዘገባ ማቅረብ ይጠበቅበታል። በዘገባውም ላይ መግቢያ፤ ሀተታና መደምደሚያ ሊያካትት ይገባል።

 Kunskapskrav för betyget D i slutet av årskurs 9

ይህን ውጤት ለማግኘት የ E መስፈርቶችና ወደ C የሚያሻግሩ ከፊል መመዘኛዎች መሟላት ይኖርባቸዋል።

 Kunskapskrav för betyget C i slutet av årskurs 9

  • ተማሪው የተለያዩ ጽሁፎችን አሳምሮ ማንበብ ይጠበቅበታል። ጽሁፎቹ ከተዘጋጁበት አላማም አንጻር መልእክታቸውን መገንዘብ ይጠበቅበታል።
  • ያንድን ጽሁፍ ይዘት ከጊዜና ከአላማ አኳያ መገምገም መቻል ይጠበቅበታል፡፡
  • የአማርኛ ቋንቋን ባህርያት ባገናዘበ መልኩ የተቀናበረ ጽሁፍ ማሰናዳት ይጠበቅበታል፡፡
  • ለተለያየ አላማ ሊውሉ የሚችሉ ጽሁፎችን በሚገባ ማቀናበር ይጠበቅበታል።
  • አላማ ገብ የሆነ ውይይት፤ ክርክር ማድረግ ይኖርበታል።
  • የበሰሉ አስተያየቶችን መሰንዘር፤ ጥያቄዎችንም ማቅረብ መቻል ይኖርበታል።
  • ሻል ባለ መንገድ ንጽጽሮችን ማቅረብ፤ ማጠቃለያዎችን መሰንዘር ይጠበቅበታል።

Kunskapskrav för betyget B i slutet av årskurs 9

  • ይህን ውጤት ለማግኘት የ C መስፈርቶችና ወደ A የሚያሻግሩ ከፊሌ መመዘኛዎች መሟሊት ይኖርባቸዋሌ።

 Kunskapskrav för betyget A i slutet av årskurs 9

  • ተማሪው የተለያዩ ጽሁፎችን በጣም በተሻለ መንገድ አንብቦ መረዳት ይጠበቅበታል።
  • ጽሁፎቹ የተቀነባበሩበትንም ስልት መለየት መቻል ይኖርበታል።
  • የጽሁፎችን ላዕላያዊ ይዘት ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ ይዘታቸውንም ፈልፍሎ ማውጣት ይጠበቅበታል።
  • ግልጽነት ያላቸውን ጽሁፎችን በሚገባ ማቀናበር ይጠበቅበታል። ጽሁፎቹም በተለያዩ ያጻጻፍ ስልቶች የተቀነባበሩ የገላጭና የተራኪ ጽሁፍ ባህርያት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።
  • ሀሳቡን እጅግ በዳበረ መንገድ በቃል መግለጽ ይጠበቅበታል፤ አከራካሪ ሀሳቦችን መሰንዘር እንዲሁም ጥልቀት ያላቸውን አስተያየቶች ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ከቀዳሚው ደረጃ እጅግ ሊቅ ባሇ መንገድ ሀሳቡን በቃሌ ማቅረብ፤ ሪፖርት ማሰማት ይኖርበታል።
  • ቋንቋው የሚነገርበትን አካባቢያዊ እና ባሕላዊ ሁኔታዎች ከስዊድንኛ ቋንቋ ባህርያት ጋር ተዛምዶ ባለው መንገድ አነጻፅሮ ትንታኔ መስጠት ይኖርበታል፡፡